Sat. Oct 24th, 2020

ድርጅቱ ከ550 በላይ ኮንቴነሮችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ አነሳ

ከ550 ኮንቴነር በላይ መድኃኒቶች እና የሕክምና ግብዓቶች ከሞጆ ደረቅ ወደብ ማንሳቱን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ገለጸ።

የድርጅቱ የመድኃኒት ኮንትራት አስተዳደር ባለሙያ ወይዘሮ አጋር ተስፋዬ፥ ከሞጆ ደረቅ ወደብ የተነሱት የጸረ ኤች.አይ.ቪ፣ የኢንፌክሽን፣ የስነ ተዋልዶ፣ የውስጥ ደዌ መድሃኒቶች እና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።


ከሞጆ ደረቅ ወደብ እንዲነሱ የተደረጉ ከ25 ዓይነት በላይ መድኃኒቶችም በተለያዩ ቅርንጫፎችና በዋናው መስሪያ ቤት የመድኃኒት ማከማቻ ገብተዋል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ከባንክ የኦርጅናል ዶክመንት መዘግየት ጋር በተያያዘ ከሞጆ ደረቅ ወደብ መድኃኒቶችን በወቅቱ ለማንሳት እክል ይገጥም እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይ ግን ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በችግሮቹ አፈታት ዙሪያ ውይይቶች ከተካሄዱ በኋላ ችግሮቹን መፍታት መቻሉን አንስተዋል።

በቀጣይም መሰል ችግሮች እንዳይከስቱ በባንኩ፣ በሞጆ ደረቅ ወደብ፣ በኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት መካከል ውል ለመፈራረም በዝግጅት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ውሉ ለድርጅቱ ተልዕኮ ቅድሚያ በመስጠት ስራዎችን ለማሳለጥ የሚያስችል እንደሆነ ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

%d bloggers like this: