Sat. Oct 24th, 2020

የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ሳተላይት ስርጭት ጀመረ

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ‹‹ኢትዮ ሳት›› በሚል ስያሜ የሳተላይት ቴሌቪዥን አገልግሎት መስጠት መጀመሯን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ማህበራት ዘርፍ አስታወቀ።

የብሮድካስት ማህበራቱ ዘርፍ ዋና ሰብሳቢ አቶ አማን ፍሰሀጺዮን ትናንት በእስካይ ላይት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኤስ ኢ ኤስ ከተባለ ዓለም ዓቀፍ የሳተላይት ካምፓኒ ጋር በመተባበር የመጀመሪያው የቴሌቪዝን ሳተላይት አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አድርገዋል።


በኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማሕበር፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንና በኤስ ኢ ኤስ ሳተላይት ካምፓኒ ትብብር እውን የተደረገው ይህ የቴሌቪዥን ሳተላይት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው አቶ አማን ገልጸዋል።

ቀደም ሲል የዓረብ እና የናይል ሳተላይትን በመጠቀም ከፍተኛ ወጪ እንደሚወጣና ጥራት ያለው አገልግሎት ማግኘት እንደማይቻል የተናገሩት ዋና ሰብሳቢው አሁን ግን እነዚህን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችል አቅም እንደተፈጠረ አስረድተዋል።

%d bloggers like this: