Sat. Oct 24th, 2020

ውዳሴ ዲያግኖሲቲክ ከሰራተኞቹ መካከል 63 በመቶ ሴቶች መሆናቸው ገለጸ

ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ካሉት ሰራተኞች መካከል 63 በመቶ ሴቶች መሆናቸውን በዚህም 2011 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት የስንዱ ዋንጫ ተሸላሚ እንደሆ ተገልጿል፡፡

ይህም ሐምሌ 22 ቀን በሂልተን ሆቴል ውዳሴ ዲያግኖስቲክ 10ኛ ዓመቱን ባከበረበት ወቅት ተገልጿል፡፡


ማዕከሉም በአሁኑ ወቅት እህት ድርጅቶችን በሥሩ ያፈራ ሲሆን በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው ‹‹ ጆርጎ አካዳሚ›› ትምህርት ቤት ፣ ‹‹ አኮ ቡና ›› ‹‹ኤልስሜድ›› እና ‹‹ ውድ ቴክ›› ናቸው፡፡ በዚህም ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩት በአጠቃላይ በቋሚና በጊዜያዊነት ከ 350 በላይ ለሚሆኑ የስራ እድል ሊፈጥር እንደቻለ ተነግሯል፡፡

በተለያዩ የሥራ ዘርፍ እና የአመራር ቦታዎች ላይ ሴቶች ለማበረታታትና አሁን በመላው ዓለም ትኩረት የተሰጠው ሴቶችን የማብቃት ስራ በድርጅቱ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ከነዚህም በተጨማሪ ከድርጅቱ መርሆዎች መካከል አንዱ የሆነው “ሰራተኞችን ማብቃት” መሆኑን የውዳሴ ዲያግኖሲቲክ ማኔጀር ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ሁይሉ ለሞላ መልቲ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

በንግግራቸውም ለሰራተኞቹ ዘወትር ሰኞ ሰኞ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር አሰልጣኖች ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸው ሰራተኞቹ ከስራም አልፎ ለህይወታቸው እንደሚጠቅማቸው አክለው ገልጸዋል፡፡

እንደ ከዚህ ቀደሙ ማዕከሉ እንደሚያደርው ጳግሜ ወር ላይ ህብረተሰቡ “ጳጉሜን ለጤና” ቅድሚያ ምርመራ መደረግ እንዳለበት እንዲገነዘብ በሚል ነፃ ምርመራ አገልግሎት እንደሚሰጠ አስታውቋል፡፡

%d bloggers like this: