Sat. Oct 24th, 2020

ቶታል የሞተር ዘይት መለወጫ ጣቢያዎች አስገነባ

ቶታል ኢትዮጵያ በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ 52 የተሽከርካሪዎች የሞተር ዘይትና የቅባት መለዋወጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባና ክልል ከተሞች መገንባቱን አስታወቀ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአዲስ አበባ 32፣ በክልል ከተሞች 20 የሞተር ዘይትና የቅባት መለወጫ ጣቢያዎችን ከሽያጭ ወኪሎች ጋር በመተባበር በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን ኩባንያው አስታውቋል፡፡ እያንዳንዱ ጣቢያ በአማካይ ለአሥር ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡


ቶታል ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ አቶ ኤርሚያስ ይስሃቅ ከተባሉ የሽያጭ ወኪል ጋር በመተባበር በአራት ሚሊዮን ብር ያስገነባውን የሞተር ዘይትና የቅባት ሽያጭ ማዕከል፣ ማክሰኞ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም. አስመርቋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1950 የተመሠረተው ቶታል ኢትዮጵያ ላለፉት 69 ዓመታት የነዳጅ ውጤቶች፣ ዘይትና ቅባት ሲያከፋፍል ቆይቷል፡፡ በ2006 ዓ.ም. የሞቢል ኩባንያ ከኢትዮጵያ ሲወጣ የኩባንያውን ንብረቶችና ንግዱን ጠቅልሎ መግዛቱ ይታወሳል፡፡ ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ 153 የነዳጅ ማደያዎች ሲኖሩት፣ 17 በመቶ የገበያ ድርሻ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡

%d bloggers like this: