Sat. Oct 24th, 2020

በባሕር ዳር ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ተያዘ

በባህር ዳር ከተማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን የአማራ ክልል አድማ ብተና 2ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል ምክትል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ ዳኛ አስታወቁ።

ምክትል ኢንስፔክተሩ ለአብመድ እንደተናሩት በ20 ጆንያዎች የተቋጠረ 497 ሽጉጥ እና ወደ 46 ሺህ የሚገመት ጥይት በባሕር ዳር ከተማ ተይዟል።


የጦር መሳሪያው ከብሔራዊ መረጃ ደህንነትና ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ከነዳጅ ጋር ተቀላቅሎ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በገባ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ውስጥ ሲጓጓዝ ነው የተያዘው።

ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተደረገ ክትትልም መሳሪያው ባሕር ዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ መያዙን ተናግረዋል።

አሽከርካሪው ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ያስታወቁት ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ ፥ ነዳጁ ከባሕር ዳር አልፎ የሚሄድ እንደነበርና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያውን ከቦቴው ለማውጣት የሚያገለግል ብረት በተሽከርካሪው ውስጥ መገኘቱን ገልጸዋል።

%d bloggers like this: