Mon. Jul 6th, 2020

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዙሪያ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አደራሽ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከልማት አጋሮችና ከዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ ጋር የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የውይይት መድረኩን በንግግር ከፍተዋል፡፡


ኢኮኖሚያዊ ገጽታውን ለመለወጥ የተከናወኑትን አንዳንድ ቁልፍ ክንውኖችን አስታውሰዋል፡፡

የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው አጀንዳ ኢትዮጵያን በ 2030 የአፍሪካ ብልጽግና ምልክት እንድትሆን የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህንኑም ለማሳካት የልማት አጋሮች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ በበኩላቸው የሃገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው የስራ እድል ፈጠራን ለመሻሻል እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ሁሉን አቀፍ እድገት ለማምጣት፣ የድህነት ቅነሳ ለማድረግ እና ሀገሪቱን ለመበልጸግ የምትችልበትን መንገድ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

%d bloggers like this: